Arts TVArts TV
← NewsLegal

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ ተስፋዬ ኡርጌና አቶ ማርክስ ፀሃዬ ላይ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ አጠናቆ እንዲያቀርብ የ10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ

Arts TV · ጃን 3 2019

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ ተስፋዬ ኡርጌና አቶ ማርክስ ፀሃዬ ላይ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ አጠናቆ እንዲያቀርብ የ10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ ተስፋዬ ኡርጌና አቶ ማርክስ ፀሃዬ ላይ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ አጠናቆ እንዲያቀርብ የ10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደrnrnበከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩትን አቶ ተስፋዬ ኡርጌና አቶ ማርክስ ፀሃዬን ጉዳይ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት በትናንትናው ዕለት ተመልክቷል፤rnrnከትናንት በስቲያ ጀምሮ የግራ ቀኙን ክርክር ከመርማሪ ፖሊስ ጅምር የምርመራ መዝገብ ጋር መዝኖ ያየው ችሎቱም፥ ከተስፋዬ ኡርጌ ጋር በተያያዘ አመልካች በተገቢ መልኩ ሪፖርት አላቀረበም፤ ይህም በተጠርጣሪው ላይ እሰራዋለሁ ያለውን ስራ በአግባቡ አለማከናወኑንና የተጠርጣሪውን የመከላከል ዕድል ማጥበቡን ተመልክቷል።rnrnፖሊስ ባቀረባቸው ማስረጃዎች ውስጥም ተጠርጣሪው ሰብዓዊ መብትን ባላከበረ መልኩ ምርመራ ያደርጉ እንደነበርና  በስውር እስር ቤት ይገለገሉ እንደነበር ችሎቱ መረዳቱን አስታውቋል።rnrnተጎጂዎችን ለማናገርም በከፊል በክልል ከተሞች የሚገኙ በመሆናቸው እና ይህንን ማድረጉም የምርመራ መዝገቡን ለማጠናቀቅ ስለሚያስችል ለመርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገዋል ሲል ችሎቱ ወስኗል።rnrnችሎቱ ከተጠርጣሪው ጋር በማይገናኙ ጉዳዮች ለጊዜ መጠየቂያነት የቀረቡ ምክንያቶችን ውድቅ በማድረግ  ከተጠየቀው የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውስጥ ከታህሳስ 22 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ የ 10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።rnrnከማርክስ ፀሃዬ  ጋር በተያያዘም ተከናወኑ የተባሉትም ሆነ ቀሪ ስራዎች ከሌላ መዝገብ ተገልብጠው መቅረባቸውን ችሎቱ የተገነዘበ ሲሆን ፖሊስ ትኩረት ሰጥቶ እንዳልሰራ የሚያሳይ መሆኑን በመጥቀስ፤ በቀጣይም  ከዚህ አይነት ስራ እንዲቆጠብ ችሎቱ አሳስቧል።rnrnበተጠርጣሪው ላይ ከተሰሙ አምስት ምስክሮች ውስጥ አራቱ  ተጠራጣሪው ያለአግባብ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ፣ በድብቅ አስር ቤት እንዲቆዩና በሃይል ምርመራ እንዲደረግባቸው ያስደርጉ እንደነበር መመስከራቸውን ችሎቱ ተረድቷል።rnrnስለሆነም መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ የሁለቱን ተጠርጣሪዎች የምርመራ መዝገብ አጠናቆ እንዲያቀርብ ለጥር 2 ቀን 2011 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል ፋና ዘግቧል።rnrn rnrn 

More in Legal