Arts TVArts TV
← NewsHealth

የጤና ፖሊሲ ክለሳ መጨረሻ  ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

Arts TV · ኤፕሪ 1 2019

የጤና ፖሊሲ ክለሳ መጨረሻ  ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የጤና ፖሊሲ ክለሳ መጨረሻ  ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡rnrnሚኒስቴሩ ይህንን የገለጸዉ በጤና ፖሊሲ ማሻሻያ ላይ ዉይይት በተደረገበት ወቅት ነዉ፡፡rnrnውይይቱን በንግግር የከፈቱት የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ የጤና ፖሊሲው እንዲሻሻል ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ሲሠራበት የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የመጨረሻውን ምዕራፍ የባለድርሻ አካላት ውይይት እያደረጉበት ነው ብለዋል፡፡rnrnቀደም ሲል አገልግሎት ላይ የቆየው የጤና ፖሊሲ ከ25 አመት በላይ የሆነው ሲሆን አሁን ካለውና ወደፊት ለሚሆነው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ፖሊሲውን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል ሚኒስቴር ዴኤታዋ፡፡rnrnየጤና ፖሊሲ የክለሳ መድረክ ላይ የሙያ ማህበራት፣ የዩኒቨርሲቲ ተወካዮች እና የግሉ ዘርፍ የተሳተፉ ሲሆን ከውይይቱም ፖሊሲው ይበልጥ እንዲዳብርና በቀጣይ አመታት የአገራችን የጤና ስርአት ይበልጥ በማጠናከር ጤናማ፣ምርታማና የበለጸገ ህብረተሰብ ለማየት የሚያስችል እንደሚሆን ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ተናግረዋል፡፡rnrnምንጭ ፤-የጤና ሚኒስቴርrnrn 

More in Health