የታራሚዎች ሰብአዊ መብት አያያዝ ለውጥ ማሳየቱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀrnrnባለፉት ስድስት ወራት የታራሚዎች ሰብአዊ መብት አያያዝ ለውጥ ማሳየቱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ።rnrnየፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ጀማል አባሶ የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀሙን በማስመልከት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡተ መግለጫ እንደተናገሩት፥በባለፉት 6 ወራት የታራሚዎች የሰብአዊ መብት አያያዝ እና ተቋማዊ መዋቅሩ መሻሻል አሳይቷል።rnrnበታራሚዎች እና በጥበቃ አባላት መካከል የነበሩ አለመግባባቶችን ወደ መልካም ግንኙነት ከመቀየር አንስቶ እስከ ከፍተኛ አመራሩ የስነ ምግባር ለውጥ ለመፍጠር ያስቻሉ ስልጠናዎች መሰጠታቸውንም አመላክተዋል።rnrnበሌላ በኩል የተቋሙን የፍትህ ስርአት ከማሻሻል አኳያ ከላይ እስከ ታች በ103 አመራር ላይ የመተካካት ስራ መሰራቱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።rnrnየፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር መመስረቻ አዋጅን ጨምሮ 34 የተለያዩ አዋጆች፣ መመሪያ እና ደንቦች ላይም ጥናት የተካሄደ ሲሆን፥ በቅርቡ ይፀድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አቶ ጀማል ጠቅሰዋል።rnrn rnrn
← NewsLegal
የታራሚዎች ሰብአዊ መብት አያያዝ ለውጥ ማሳየቱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ
Arts TV · ጃን 10 2019






