ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ከንግድ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ሰሞኑን በተፈጠረው የነዳጅ እጥረት ዙርያ ከማደያ ባለቤቶችና ከነዳጅ አቅራቢ ተቋማት ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡rnrn
rnrnምክትል ከንቲባው በወይይቱ ወቅት የነዳጅ እጥረት የተፈጠረው ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው ነው ብለዋል፡፡rnrnዘርፉ የረጅም ጊዜ መፍትሄ የሚሹ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ የከተማው አስተዳደር፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ያካተተ ግብረ-ሃይል በማቋቋም ገበያውን በቋሚነት የማረጋጋት ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡rnrnየከተማ አስተዳደሩ እንዳለው ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን በከተማዋ ውስጥ ያሉትን በነዳጅ ማደያ ዴፖዎችን ላይ ፍተሻ ያካሂዳል፡፡rnrnበማከማቻ ስፍራዎች በቂ ነዳጅ እያለ እጥረት የተፈጠረ በማስመሠል ህብረተሰቡን የሚያጉላሉና ችግር እየፈጠሩ ያሉ ማደያዎች እና የነዳጅ አቅራቢ ተቋማት ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል ሲል የከንቲባ ፅ/ቤት መረጃውን በድረ ገፁ አስፍሯል፡፡rnrnበሌላ የፅህፈትቤቱ መረጃ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የሪል ስቴት አልሚዎችን የሚፈትሽ ግብረ-ሀይል ተቋቁሟል፡፡rnrnምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በትናትናው ዕለት ከሪል ስቴት አልሚዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በዘርፉ የሚታዩትን የአሰራር ችግሮች የሚፈትሽ ግብረ-ሃይል እንደሚቋቋም እና የሪል እስቴት ዘርፉ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ደጋፊ እንደመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ህጋዊ የሆኑትን እንደሚደግፍም አስታውቀዋል፡፡rnrn
rnrnየሚቋቋመው ግብረ ሀይል በዋናነት በሪል እስቴት ኢንዱስትሪው ላይ የሚታዩትን ችግሮች የሚፈትሽ ሲሆን ከፕላን፣ ከካርታ፣ ከሊዝ እና መሬትን በህገ-ወጥ መንገድ አጥሮ ያስቀመጡትን እንደሚፈትሽ አስታውቀዋል፡፡rnrn
rnrnከንቲባው በመንግስትም በኩል ያሉ አስተዳደራዊ ችግሮች እንደሚፈተሹም ጨምረው ገልፀዋል፡፡