ናይጄሪያዊው መንገደኛ ህገወጥ ገንዘብ ይዞ ከሀገር ሊወጣ ሲል ተያዘ
rnአርትስ 21/04/2011rnrn ተጠርጣሪ ኢፋኒቸኩ አማኑኤል ኢኬዲቡ የተባለ ናይጀሪያዊ መንገደኛ፤ ህገወጥ 141ሺህ ዶላር ይዞ በቦሌ ኤርፖርት በኩል አድርጎ ወደ ናይጀሪያ ሊወጣ ሲል ታኅሣሥ 20/2011 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር መዋሉን በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን የቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡rnrnናይጀሪያዊው መንገደኛ ህገወጥ ገንዘቡን ይዞ ሲንቀሳቀስ በኤክስሬይ የፍተሻ ማሽን አማካኝነት፣ በጉምሩክ ሠራተኞች እና በብሔራዊ መረጃ ደኅንነት ባለሙያዎች ከፍተኛ አስተዋጾ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩ ተይዟል፡፡rnrnቅ/ፅ/ቤቱ እያደረገ ያለው ክትትል እና ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያሳወቀ ሲሆን በቀጣይ ህብረተሰቡ ህገወጦችን በንቃት በመከታተል ለህግ እንዲያቀርቡ በማድረግ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡