አርትስ 20/02/18
rይህ የተባለው የአፍሪካ ህብረትና የአሜሪካ መንግስት በጥምረት ባዘጋጁት ”ጥቃት ተኮር ጽንፈኝነትን የመከላከል ሳምንት” የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
rትላንት በአዲስ አበባ በይፋ የተጀመረው ለተከታታይ ሰባት ቀናት በሚቆየው ጥቃት ተኮር ጽንፈኝነትን የመከላከል ሳምንት ከሽብርተኝነትና ጽንፍ ከረገጡ አስተሳሰቦች የሚመነጩ ሌሎች ጥቃቶችን መዋጋትበሚቻልበት መንገድ ላይ ውያያት እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡
rመተባበር በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ኩነቶች የሚከበረውን ይህንኑ መድረክ በተመለከተ በአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ክፍል ተወካይ ወይዘሮ ኢናስ ሙሃመድ እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅትበመካከለኛውና በምዕራብ አፍሪካ አገሮች ቦኮሃራም፤ በሰሜንና በምስራቅ አፍሪካ አካባቢዎች ደግሞ አይኤስ እና አልሸባብ ስጋት ናቸው ብለዋል።
rበሌላ በኩል በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ብሄርና ጎሳ ተኮር የሆኑ ጥቃቶች እንደዚሁም ፖለቲካን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች በርካታ ዜጎችን ለህልፈት እየዳረገ ነው ብለዋል።
rሽብርተኝነት እንዲቀንስ፣ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እንዲሁም የዴሞክራሲ ባህል እንዲዳብር የአፍሪካ ህብረት በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
rበአሜሪካ የፀረ-ሽብር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሚስ አሊና ሮማኖቪስኪ በበኩላቸው በአፍሪካ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ጠንካራ አቅምና የፍትህ ሥርዓት ያላቸው መንግስታት እንዲፈጠሩ አሜሪካ የማያቋርጥድጋፍ እንደምታደርግ ቃል ገብተዋል።





