Arts TVArts TV
← NewsLegal

በቦሌ ክፍለ ከተማ በጦር መሳሪያ የተደገፈ ዘረፋ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ፡፡

Arts TV · ጃን 3 2019

በቦሌ ክፍለ ከተማ በጦር መሳሪያ የተደገፈ ዘረፋ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ በጦር መሳሪያ የተደገፈ ዘረፋ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ፡፡rnrnየአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀዉ ቁጥራቸው 24 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ማክሰኞ ከሌሊቱ 7፡20 የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 30212 ኦ/ሮ አይነቱ ሚኒባስ በሆነ ተሸከርካሪ ተሳፍረው ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ፤ፖሊስ አስቀድሞ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት እና ባደረገው ክትትል በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስፍራው ሰሚት ሴንተራል ሆቴል አካባቢ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡rnrnየሰሚት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ም/ኮማንደር ካሳሁን ፍቃዱ እንደተናገሩት ተጠርጣሪዎቹ በተያዙበት ወቅት አንድ ሽጉጥ ከመሰል ስምንት ጥይት ጋር ፣ ሁለት ፓውዛ መብራቶች ፣ የብረት መቁረጫ መቀስ ፣ 20 ማዳበሪያዎች እና ከተር በኢግዚቢትነት ተይዞ ፖሊስ ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ከኃላፊው ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡rnrnከዚህ ቀደም በቦሌ ክፍለ ከተማ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ለግንባታ የሚውሉ ልዩ ልዩ የኤሌትሪክ ገመዶችን የሰረቁ ተጠርጣሪዎች በህብረተሰቡ ትብብር ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ም/ኮማንደር ካሰሁን ተናግረው ፤ለፖሊስ ስራ ስኬታማነት ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ቀና ትብብር አድንቀዋል፡፡rnrn rnrn 

More in Legal