ሪያድና ዋሽንግተን ግንኙነታቸው ነፋስ ገብቶበታል
rnአርትስ 12/03/2011rnrnየሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲ አይ ኤ በጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ ዙሪያ ያወጣውን ሪፖርት መሰረተ ቢስ ነው ብሎታል፡፡rnrnሮይተርስ እንደዘገበው የሳውዲ መንግስት ጋዜጠኛው እንዲገደል ልኡል አልጋ ወራሽ ሞሀመድ ቢን ሳልማን ትእዛዝ ሰጥተዋል የሚለውን የአሜሪካን መግለጫ በፅኑ ተቃውሞታል፡፡rnrnየሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብደል አል ጁቢር በአልጋ ወራሹ ላይ የሚነዛውን አሉባልታ አጥብቀን እንቃወማለን በማለት አልሻርቅ አል ዋስት ለተባለው ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡rnrnባለፈው ሳምንት የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ሲአይኤን ጠቅሰው ባሰራጩት ዘገባዎቻቸው የካሾጊ ገድያ ከሳውዲው ንጉስ ጋር የተገናኘ መሆኑን መዘገባቸው በሪያድ ላይ ዓለም አቀፍ ተቃውሞን አስከትሎባታል፡፡