Arts TVArts TV
← NewsLegal

ሜጀር ጄኔራል ክንፈን ጨምሮ ስምንት ተከሳሾች ከ319 ሚሊየን ብር በላይ በማባከን ክስ ተመሰረተባቸው

Arts TV · ጃን 11 2019

ሜጀር ጄኔራል ክንፈን ጨምሮ ስምንት ተከሳሾች ከ319 ሚሊየን ብር በላይ በማባከን ክስ ተመሰረተባቸው

ሜጀር ጄኔራል ክንፈን ጨምሮ ስምንት ተከሳሾች ከ319 ሚሊየን ብር በላይ በማባከን ክስ ተመሰረተባቸውrnrnየቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር የነበሩትን ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ በስምንት ግለሰቦች ላይ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ከ319 ሚሊየን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ሲል ክስ መስርቷል፡፡rnrnስምንቱ ተከሳሾች ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም  ወንጀል ሰባት ክሶች ቀርቦባቸዋል፡፡rnrnበክስ ሰነዱ ላይ እንደተመላከተው ክሱ የተፈፀመው  በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የአዳማ እርሻ መሳሪያዎች ኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውሉ ትራክተር እና የትራክተር ተሳቢዎች ግዥ ያለግልፅ ጨረታ፣ ያለግዥ ፍላጎት እና ለሁሉም አቅራቢዎች እኩል እድል ባልሰጠ መልኩ ተካሂዷል በሚል ነው፡፡rnrnበዚህም መንግስት ከገበያ ውድድር ሊያገኝ የሚችለውን የጥራት፣ የዋጋና የአቅርቦት ጥቅም ጎድተዋል ያለው ከሳሽ አቃቢ ህግ ይህንም ለማስረዳት የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን ማሰባሰቡን ዐቃቢ ህግ በክስ ዝርዝሩ አያይዞ አቅርቧል።rnrnተከሳሾች የክስ መዝገቡ ችሎቱ ላይ ስለደረሳቸው በጠበቆቻቸው አማካኝነት መቃወሚያቸውን ለማቅረብ ተለዋጭ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቀዋል፡፡rnrnአቃቢ ህግም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎች በአማርኛ ተተርጉመው በ10 ቀናት ውስጥ ለፍርድ ቤቱ እንዲቀርቡም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡rnrnፍርድ ቤቱም ለጥር 17 ቀን 2011 አመተ ምህረት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡rnrn

More in Legal