ጊኒ ዎርምን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የአመራር አካላት ቁርጠኝነት ይፈለጋል ተባለ
rnአርትስ 03/04/11rnrnrnይህንን ያሉት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ናቸው።rnrnየጊኒ ዎርም በሽታን ለማጥፋት እየተከናወኑ ያሉትን ስራዎችን የሚገመግው 23ኛው ሀገር አቀፍ ዓመታዊ እቅድ የአፈፃፀም ግምገማ ትናንት በጋምቤላ ከተማ ተጀምሯል።rnrnሚኒስትሩ በዚሁ ግምገማ ላይ እንዳሉት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በጤናው ዘርፍ በርካታ ውጤቶች ቢመዘገቡም የጊኒ ዎርም በሽታን በማጥፋት ረገድ የተከናወኑት ስራዎች ዝቅተኛ ናቸው።rnrnጊኒ ዎርም ከኢትዮጵያና አራት ሃገራት በቀር በየትኛውም የዓለም ሃገር የሌለ በሽታ ነው ብለዋል።rnrnበሽታው ከኢትዮጵያ ሊጠፋ ያልቻው በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት በቁርጠኝነት፣ ተቀናጅቶ ያለመስራትና የምርምርና ጥናት ስራዎች ችግሮች መሆናቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።rnrnየጊኒ ወርም በሽታን በ2019 ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።rnrn
rnrn
rn





