Arts TVArts TV
← NewsHealth

ጉዳት የደረሰባቸዉን  የአካል ክፍል  የሚተኩ (የአካላዊ ተሃድሶ ህክምና በሁሉም መንግስት ጤና ተቋማት  ሊሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

Arts TV · ኤፕሪ 18 2019

ጉዳት የደረሰባቸዉን  የአካል ክፍል  የሚተኩ (የአካላዊ ተሃድሶ ህክምና በሁሉም መንግስት ጤና ተቋማት  ሊሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ጉዳት የደረሰባቸዉን  የአካል ክፍል  የሚተኩ (የአካላዊ ተሃድሶ ህክምና በሁሉም መንግስት ጤና ተቋማት  ሊሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡rnrnቀደም ሲል በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ስር የነበሩ የአካላዊ ተሃድሶ ህክምና ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ወደ ጤና ሚኒስቴር እንዲዛወሩ በተገባው ውል መሰረት የርክክብ ስራ እየተሰራ  ነዉ፡፡rnrnየጤና ሚኒስቴር የክሊኒካል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አባስ ሀሰን  በጉዳዩ ላይ በተደረገ ዉይይት ላይ  እንደተናገሩት የጤና አገልግሎት እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም የአካላዊ ህክምና አገልግሎት መካተት አለበት ብለዋል፡፡rnrnበየጤና ተቋማት የአካላዊ ተሃድሶ ህክምና ትኩረት ያልተሰጠው በመሆኑ  ታካሚዎች ህክምናው ለመውሰድ ይቸገራሉ ተብሏል፡፡rnrnበአገር አቀፍ ደረጃ 11 የአካላዊ ተሃድሶ ህክምና እየሰጡ ያሉ ማዕከላት ሲኖሩ ህክምናዉን በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎችና ጤና ተቋማት ወጥ በሆነ መንገድ ለመስጠት አራት ምዕራፎች ያሉት መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡rnrnበአገር አቀፍ ደረጃ በአካላዊ ተሃድሶ ህክምና የአለርት ሆስፒታል  ጥሩ ተሞክሮ እንዳለዉ ከጤና ሚኒስቴር ሰምተናል፡፡

More in Health