የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ተሸላሚ ሆኑ
rnአርትስ 05/04/2011rnrn ሽልማቱ በዩኒቨርሲቲው በሚዘጋጀውና በጤና ዘርፍ የአመራርነትና በጎ አስተዋጽኦ አበርክቶ ዘርፍ ላይ የሚሰጥ ሲሆን፥ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማንም የ2018 ተሸላሚ ሆነዋል፡፡rnrnከሚኒስቴሩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ እንደተገኘው መረጃ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዌስተርን ኬፕ ዶክተር አሚር አማን በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ላይ እየፈጠሩ ባሉት ተጽዕኖ ነው የሸለምኳቸው ብሏል፡፡rnrnሚኒስትሩ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስላበረከተላቸው ሽልማት በፌስ ቡክ ገጻቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡rnrnዩኒቨርስቲው በደቡብ አፍሪካና በተለያዩ ሀገራት በጤናው ዘርፍ ትምህርት በመስጠት እንዲሁም በምርምር ስራዎች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ተቋም ነው፡፡rnrn