Arts TVArts TV
← NewsHealth

የኩፍኝ በሽታ በአፍሪካ በአስር እጥፍ ጨምሯል፡፡

Arts TV · ኦገስ 13 2019

የኩፍኝ በሽታ በአፍሪካ በአስር እጥፍ ጨምሯል፡፡

የኩፍኝ በሽታ በአፍሪካ በአስር እጥፍ ጨምሯል፡፡rnrnዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት በሪፖርቱ ይፋ እንዳደረገው የኩፍኝ በሽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በሶስት እጥፍ ጨምሯል፡፡rnrnአሶሸትድ ፕሬስ የድርጅቱን ሪፖርት ጠቅሶ እንደዘገበው የበበሽታው ስርጭት በአፍሪካ ብቻ ተነጥሎ ሲታይ በአስር እጥፍ ነው የጨመረው፡፡rnrnየድርጅቱ ቃል አቀባይ ክርስቲያን ሊንድሜር ጄኔቫ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይህ ክስተት እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2006 ወዲህ የታየ ትልቅ ቁጥር ነው ብላል፡፡rnrnበሽታው በብዛት ተሰራጭቶባቸዋል ተብለው የተመዘገቡት ሀገራት ከአፍሪካ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ እና ማዳጋስካር ከምስራቅ አውሮፓ ደግሞ ዩክሬን ናቸው፡፡rnrnአንዲያም ሆኖ ማዳጋስካር በቅርብ ወራት ባደረገቸው ብሄራዊ የክትባት ዘመቻ የታማሚዎችን ቁጥር መቀነስ ችላለች ነው የተባለው፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Health