የስልጤ ዞን ምራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ነዋሪዎች ነፍሰጡር እናቶችን እየተንከባከቡ ነዉ፡፡rnrnበስልጤ ዞን ምራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ነብሰጡር እናቶች ለመውለድ ቀናቸው ሲቃረብ ቤታቸው ለጤና ጣቢያው የሚርቅ እናቶች እንዳይንገላቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ማረፊያ አዘጋጅተው እስከሚወልዱበት ቀን ድረስ እንክብካቤ ሳይቋረጥባቸው እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡rnrnከእርጉዝ እናቶች ማቆያ አገልግሎት ባሻገር በአካባቢው የሚገኙ ባለባጃጆችም በወረዳው የሚገኙ ባጃጆችን በመደራጀት ለእርጉዝ እናቶች ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡rnrnማህበረሰቡ ይህን ማቆያ አዘጋጅቶ ለእናቶች እንክብካቤ ሲያደርግ ከእለት ጉርሱ ቀንሶ እንጂ የትኛውም የመንግስት አካል ድጋፍ አላደረገለትም፡፡rnrnሰሞኑን የጤና ሚኒስቴር አመራሮች እና የሚዲያ አካላት በዚሁ ወረዳ ተገኝተው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በሌሬ ጤና ጣቢያ እናቶች ከመውለጃ ቀናቸው ቀደም ብለው የሚያርፉበት የእናቶች ማቆያ እና የአካባቢው ባለባጃጆች ትኩረትን ስበዋል፡፡rnrnበሊሬ ጤና ጣቢያ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባው የእናቶች ማቆያ ከሩቅም ከቅርብም አካባቢ የሚመጡ እናቶች ከመውለጃ ጊዜያቸው ቀደም ብለው መጥተው የሚያርፉበት ሲሆን እስከ መውለጃ ጊዜያቸውም በቤታቸው የሚያገኙት ማናቸውም ነገሮች ሳይጓደሉ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል፡፡rnrnየጤና ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ በተለይ ለህክምና ጣቢያዎች የሚርቅ መኖሪያ ቤት ያላቸው እናቶች ጤና ጣቢያ እስከሚደርሱ በወሊድ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች እንዳያጋጥማቸው እና የእናቶችን ሞት ከመቀነስ አንፃር የነዋሪዎቹ ስራዎች የሚያስደንቅ ተግባር ነው ብለዋል፡፡rnrnበተለይም እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ በባለሙያዎች የሚደረገው ክትትል ፤ ከወለዱ በኋላም ወደ ቤት መልሶ የሚያደርሳቸው የባጃጅ አገልገሎት በፈቃደኝነት በተደራጁ ወጣቶች በነጻ መሰጠቱ ለሌሎች ወረዳዎች አርአያ እንደሆነም ተናግረዋል።rnrnህብረተሰቡ በራሱ ተነሳሽነት አምቡላንስ በመግዛትና የእናቶች ማቆያ ቤቶችን በመገንባት ትልቅ ስራም ሰርቷል፡፡rnrn
← NewsHealth
የስልጤ ዞን ምራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ነዋሪዎች ነፍሰጡር እናቶችን እየተንከባከቡ ነዉ፡፡
Arts TV · ኤፕሪ 8 2019






