Arts TVArts TV
← NewsHealth

የመድሃኒት አያያዝ እና አገልግሎት አሰጣጥ ችግር በታየባቸው መድህኒት ቸርቻሪ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ  እየተወሰደ ነው

Arts TV · ፌብ 5 2019

የመድሃኒት አያያዝ እና አገልግሎት አሰጣጥ ችግር በታየባቸው መድህኒት ቸርቻሪ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ  እየተወሰደ ነው

የመድሃኒት አያያዝ እና አገልግሎት አሰጣጥ ችግር በታየባቸው መድህኒት ቸርቻሪ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ  እየተወሰደ ነውrnrnበጉዳዩ ዙሪያ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ከመድሃኒት ቸርቻሪ ድርጅቶች ጋር የዉይይት መድረክ ለካሄዷል፡፡rnrnበመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ወረቴ እንደ ናሙና በተመረጡ የከተማችን 86 መድሃኒት ቸርቻሪ ድርጅቶች ላይ በተደረገባቸው  ጥናት የመድህኒት አያያዝ፣ የአገልግሎት አሰጣጥና  ምንጫቸው የማይታወቅ መድሃኒቶችን የመጠቀም ችግሮች መኖራቸውን ማረጋገጥ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡rnrnዋና ዳይሬክተሩ  ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለህብረተሰቡ ጥራቱና ደህንነቱ እና ፈዋሽነቱ የተጠበቀ የመድሃኒት አገልግሎት ተደራሽ በማያደርጉ መድሀኒት ቸርቻሪ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

More in Health