Arts TVArts TV
← NewsHealth

የህክምና መሳሪያዎችን ከባክቴሪያ ነፃ የሚያደርግ መሳሪያ በኢትዮጵያ ሊመርት ነው፡፡

Arts TV · ፌብ 21 2019

የህክምና መሳሪያዎችን ከባክቴሪያ ነፃ የሚያደርግ መሳሪያ በኢትዮጵያ ሊመርት ነው፡፡

የህክምና መሳሪያዎችን ከባክቴሪያ ነፃ የሚያደርግ መሳሪያ በኢትዮጵያ ሊመርት ነው፡፡rnrnመሳሪያው ጋዝን ብቻ በመጠቀም የህክምና መሳሪያዎችን  ነጻ በማድረግ ለድጋሚ አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው፡፡rnአሁን ጥቅም ላይ ያሉት መሳሪያዎች በህክምና ጣቢያዎች ውስጥ ተቀምጠው ውሃና መብራትን የሚጠቀሙ ናቸው፡፡rnአይ ኤም ጂ ኢንተርናሽናል ሜዲካል ግሩፕ  በኢትዮጵ የሚያመርተዉ  ተንቀሳቃሽ መሳሪያ ግን ውሃና መብራት የማይፈልግ ሲሆን በቀላሉ ከቦታ ቦታ በማንቀሳቀስ ጥቅም ላይ የሚውል ነው ተብሏል፡፡rnመሳሪያውን በኢትዮጵያ ለማምረት የሚያስችለዉን ስምምነት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር  ሹመቴ ግዛው እና ከአይ ኤም ጂ ኢንተርናሽናል የህክምና ቡድን የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ትግስቱ  አዳሙ ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡rnተን ቀሳቃሽ  መሳሪያዉ ከኪሚካል ኢንዱስትሪዎች ጋዝ በቀላሉ ማግኘት ስለሚቻል የግብዓት ችግር እንደማይኖር ተጠቁሟል፡፡rnማንኛውንም የህክምና መሳሪያዎችን ለድጋሚ ግልጋሎት ዝግጁ የሚያደርገው ይህ መሳሪያ የውሃና መብራት እጥረት ባለበት አካባቢ የሚሰጠውን ህክምና ለማገዝ ትልቅ ሚና ስለሚኖረው ወደ ምርት እንዲገባ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገልጽዋል፡፡rnrn 

More in Health