Arts TVArts TV
← NewsHealth

ኮሮናቫይረስ ያለበት ጃፓናዊ በኢትዮጵያ መገኘቱ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታወቀ።

Arts TV · ማርች 13 2020

ሚኒስትሯ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት አንድ ከሶስት ቀን በፊት ከቡርኪናፋሶ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ጃፓናዊ ኮሮናቫይረስ ተገኝቶበታል።rnከዚህ ቀደም ብሎ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ታከለ ኡማ በትዊተር ገፃቸው ላይ አንድ ጃፓናዊ ኮሮናቫይረስ ተገኝቶበታል ሲሉ አስታውቀው ነበር።rnከንቲባው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መውሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄ በመልዕክታቸው ላይ ጨምረው አስፍረዋል።rnሚኒስትሯ እንዳሉት ጃፓናዊ ትኩሳትና ማሳል የመሳሰሉ የቫይረሱ ምልክቶችን የሚያሲይ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛል ብለዋል።<span class="text_exposed_show">rnየጤንነቱ ሁኔታም መጥፎ የሚባል አንዳልሆነ ገልፀዋል።rnከንቲባው "አንድ ጃፓናዊ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። ሁላችንም ከእጅ ንክኪዎች እና አላስፈላጊ ስብሰባዎች አንቆጠብ ለማለት እፈልጋለሁ።" በማለት ነበር መልዕክታቸውን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች መልዕክታቸውን አስፍረዋል።rn(FBC)</span>

More in Health