ከ121 በላይ የጤና ባለሙያዎች ለጌዲዮ ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረግ ተልከዋል ተባለ፡፡rnrnየጤና ሚኒስቴር ለጌዲዮ ዞን ተፈናቃዮች ድጋፍ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎችና የተለያዩ መድሃኒቶች እንዲሁም ሌሎች ግብአቶችን ወደ ስፍራው ልኳል፡፡rnrnየጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዋ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለፁት ካሁን በፊት ከክልል 10 ሐኪሞች ፣ 10 ነርሶች፣ 5 የአካባቢ ጤና ባለሙያዎች እና 5 የኢፒዲሞሎጂ ባለሙያዎች ወደ ስፍራው ተልከዋል፡፡rnrnየህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ቅኝቶችና ዳሰሳዎች እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍም ተደርጓል፡፡rnrnበዚህኛው ፕግራም ከአዲስ አበባ የተውጣጡ አምስት ሐኪሞች እና 26 ነርሶች እንዲሁም መድኃኒቶችና ሌሎች ግብዓቶች ከኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ወጪ ሆነው ወደ ስፍራው ተልከዋል ብሏ ሚኒስቴሩ፡፡rnrnሚኒስትር ዴኤታዋ ወደ ስፍራው ካቀኑት ከ121 በላይ የጤና ባለሙያዎች በተጨማሪ የተለያዩ መጠን እና አይነት ያላቸው መድሃኒቶች መላካቸውንና ይህ መሰሉ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡






