በዩጋንዳ የሞተር ሳይክል አምቡላንሶች የብዙዎችን ህይዎት እየታደጉ ነው፡፡rnrnበርካታ ዩጋንዳዊያን በመንገድ ችግር ሳቢያ የአምቡላንስ አገልግሎት ስለማያገኙ የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል፡፡rnrnይህን የተረዳው በሀገሪቱ የሚንቀሳቀስ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በብስክሌቶች እና በሞተር ሳይክሎች የሚጎተቱ አምቡላንሶችን በማዘጋጀት አገልግሎት መስጠት ጀምራል፡፡rnrnበዚህ አገልግሎቱም በተለይ ነፍሰ ጡር ሴቶች የቅድመ ወሊድ ክትትል ለማድረግ እንዲሁም ከወሊድ በኋላ የጤናቸውን ሁኔታ እንዲከታተሉ በእጅጉ አግዟቸወዋል ነው የተባለው፡፡rnrnሳንድራ ናይጋጋ የባለች ነፍሰ ጡር እነዚህን አምቡላንሶች ባታገኝ ኖሮ አደገኛ የጤና ችግር ላይ ልትወድቅ ትችል እንደነበር ገልፃ ይህ ግብረ ሰናይ ተቋም ላደረገላቸው ሁሉ ምስጋናዋን አቅርባለች፡፡rnrnአብዛኞቹ የዩጋንዳ አካባቢዎች ከዋና ዋና መንገዶች ጋር በመንገድ ስላልተገናኙ በትራንስፖርት ችግር በቀላሉ ታክመው የሚድኑ ሰዎች ህይዎታቸው እንደሚያልፍ ይነገራል፡፡rnrnአልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው በዩጋንዳ በየቀኑ ከ15 የማያንሱ ሴቶች ከወሊድ ጋር በተያየዘ ችግር ለሞት ይዳረጋሉ፡፡rnrn rnrnመንገሻ ዓለሙ






