አርትስ 20/03/2011rnrnለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ ሁለት መንገዶች የተለዩ ሲሆን አንደኛው ከጊዮርጊስ አደባባይ- በቸርችል ጎዳና-ኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከጊዮርጊስ አደባባይ -በ6ኪሎ-በ5ኪሎ አድርጎ መድረሻውን ጊዮርጊስ አደባባይ ያደርጋል፡፡rnrnየአዲስ አበባ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከአዲስ አበባ ስፖርትና ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በመሆን በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶክተር ሳሙኤል ዘ/መንፈስ ቅዱስ ፤የስኳር፣የደም ግፊት እና የጡት ካንሰር ነጻ የምርመራ አገልግሎትም ይሰጣል ብለዋል፡፡rnrnበእለቱ የህብረተሰቡን የጤና ግንዛቤ ለማሳደግ የተለያዩ የጤና መልእክቶች ይተላለፋሉ፡፡rnrnበአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ውድድርና ተሳትፎ ባለሙያ አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል በበኩላቸው በእለቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመሩ የአካል ብቃት ባለሙያዎችም እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡rnrnየፊታችን ህዳር 30 በሚካሄደው ከትራፊክ ፍሰት ነጻ ቀን የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ዲፕሎማቶች የሚሳተፉበት ሲሆን ፤በዕለቱ ከ3ሺ እስከ 5ሺ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡rnrnፕሮግራሙም ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት የሚካሄድ መሆኑንም ታውቋል፡፡rnrn
← NewsHealth
በአዲስ አበባ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ከትራፊክ ፍሰት ነፃ የሆነ ቀን ለማክበር ሚዘጉት መንገዶች ይፋ ሆኑ
Arts TV · ኖቬም 29 2018





