Arts TVArts TV
← NewsHealth

በበጀት ዓመቱ የጤና መሰረተ ልማት ግንባታዎች አፈጻጸም አበረታች ነው ተባለ::

Arts TV · ፌብ 18 2019

በበጀት ዓመቱ የጤና መሰረተ ልማት ግንባታዎች አፈጻጸም አበረታች ነው ተባለ::

በበጀት ዓመቱ የጤና መሰረተ ልማት ግንባታዎች አፈጻጸም አበረታች ነው ተባለ::rnrnጅማ ከተማ ላይ ሲካሄድ በነበረው የጤና ተቋማት ግንባታ አፈጻጸም ግምገማ ላይ አማራ፣ ሶማሌ፣ አፋር ክልልና እና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የተሻለ አፈጻጸም እንዳሳዩ ተነግሯል።rnrnበጤና ሚኒስቴር የጤና መሠረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታደሠ የማነ በግምገማዉ ወቅት እንደተናገሩት፤ የአገልግሎትና የጥራት ችግር ያለባቸውን 200 ጤና ጣቢያዎችን የማስፋፋት፣ የውሃና የመብራት ችግር ያለባቸውን 200 ጤና ጣቢያዎችን የማሟላት እንዲሁም ለ170 ጤና ጣቢያዎች ከፀሃይ ሃይል መብራት የማቅረብ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነዉ ።rnrnበአገር አቀፍ ደረጃ በበጀት ዓመቱ ጠረፋማ ለሆኑ ጤና ጣቢያዎች 2500 የመኖሪያ ቤት ግንባታዎችም አየተሰሩ ነዉ፡፡rnrnየግንባታ መዘግየቶች መኖራቸውን፣ በግንባታ ግብዓቶች ወጪ መጨመር፣ የዉጭ ምንዛሬ እጥረት ፤ በአንዳንድ ክልሎች የነበረው የጸጥታ ችግር ፣ የስራ ተቋራጮች ድክመት እና የአማካሪ ድርጅቶች የክትትል ማነስ፣ እንደችግር ተነስተዋል፡፡rnየአፈጻጸም ችግር ያለባቸውን ተቋራጮች እና አማካሪ ድርጅቶች ውልን በማቋረጥ፣ በህግ እንዲጠየቁ እና በቀጣይም በግንባታው ዘርፍ በጨረታ የማይወዳደሩትን የመለየት ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል  በመፍሄነት ተቀምጧል ።

More in Health