Arts TVArts TV
← NewsHealth

በርካታ ኮንጓዊያን ኢቦላ አለ ብለው እንደማያምኑ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

Arts TV · ማርች 28 2019

በርካታ ኮንጓዊያን ኢቦላ አለ ብለው እንደማያምኑ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

በርካታ ኮንጓዊያን ኢቦላ አለ ብለው እንደማያምኑ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡rnrnበዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ በተደረገ ጥናት ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉት ነዋሪዎች ኢቦላ በትክክል አለ ብለው አያምኑም፡፡rnrnህዝቡ ይህን እውነታ መቀበል አለመቻሉ በስራቸው ላይ ትልቅ እንቅፋት እየተፈጠረባቸው መሆኑን የጤና ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡rnrnአልጀዚራ እንደዘገበው አስካሁን በዲሞክራክ ሪፓብሊክ ኮንጎ 639 የሚሆኑ ሰዎች በኢቦላ በሽታ ህይዎታቸው ቢያልፍም ኮንጓዊያን ግን ለነገሩ ቁብ የሰጡት አይመስሉም፡፡rnrnበጥናቱ ከተካተቱት 961 ሰዎች መካከል 25 በመቶ የሚሆኑት ኢቦላ የሚባል ህመም የለም የሚሉ ሲሆኑ 45.9 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በሽታው መኖሩን ባይክዱም አሁን  ተከስቷል የሚሉት ግን የኮንጎን መረጋጋት የማይፈልጉ ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡rnrnበምስራቃዊ ኮንጎ ስራ ላይ የተሰማራው የዓለም አቀፉ የነብስ አድን ኮሚቴ አባል ጣሪቅ ሪብል የጥናቱ ውጤት እኛ በስራ ላይ የሚያጋጥመንን እውነታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው ብሏል፡፡rnrnእንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2013 እስከ 2016 ባለው ጊዜ  በምእራብ አፍሪካ ሀገራት የተከሰተው የኢቦላ ቫይረስ ከ11 ሺህ 300 በላይ ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል፡፡rnrnየዓለም የጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት በዲሞክራክ ኮንጎ በየሳምንቱ በአማካይ ቢያንስ ከስምንት ያላነሱ ሰዎች በኢቦላ ህመም እንደሚጠቁ ይፋ አድርጓል፡፡rnrn rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Health