Arts TVArts TV
← NewsFACT CHECK

ሐሰት: ይህ ምስል በደሴ በመንግሥት ኃይሎች እና በህወሓት መካከል የተተኮሱ መድፎችን አያሳይም።

Arts TV · ኦክቶ 31 2021

ሐሰት: ይህ ምስል  በደሴ በመንግሥት ኃይሎች እና በህወሓት መካከል የተተኮሱ መድፎችን አያሳይም።

ምስሉ የሩሲያ ወታደሮች በኖቮሲቢርስክ ከተማ የመድፍ ልምምድ ሱያደርጉ ያሳያል።

በመንግሥት ኃይሎች እና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አማጺያን መካከል በሚደረገው ጦርነት ምክንያት በደሴ በመሀል ከተማ የመንግስትን መድፍ ያሳያል በሚል የተለጠፈው የፌስቡክ ልጥፍ ሐሰተኛ ነው።

ልጥፉ ላይ በአማርኛ ቋኝቋ የተጻፈው መግለጫ “100,000 የደሴ ከተማ ህዝብ አስይዞ የሚጫወት መንግስት! በመሀል ከተማ መድፍ” ይላል።

n
n

ባለፉት ቀናት የደቡብ ወሎ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ደሴ አቅራቢያ ባሉ ስፍራዎች በመንግሥት ኃይሎች እና በህወሓት አማጺያን መካከል ጦርነት የተካሄደ  ሲሆን የደሴ ከተማም የመድፍ ተኩስ አስተናግዳለች።

ከዚህ ጋር ተያይዞ አሜሪካ በቃለ አቀባይዋ ኔድ ፕራይስ በኩል ጥቅምት 21፣ 2014 ዓ.ም በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ  በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት መስፋፋት አሳስቦኛል ብላለች።

ከዚህም በተጨማሪ ህወሓት በከተሞች ላይ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን እንዳይጠቀም ከማሳሰብ በተጨማሪ የኢትዮጵያ መከላከያ በመቀለና በተለያዩ የትግራይ ክልሎች የሚያደርገውንና ለበርካቶች ሞት ምክንያት የሆነውን የአየር ጥቃትም ማቆም አለበት ብላለች አሜሪካ።

ሆኖም የያንዴክስ የምስል ፍለጋ (Yandex image search) ውጤት እንደሚያሳየው ይህ ምስል እ.ኤ.አ ግንቦት 08, 2016 ከተለቀቀው የዩትዩብ ቪዲዮ ተምኔይል የተወሰደ ሲሆን ምስሉ በቪዲዮው 55ተኛ ሰከንድ ላይ ይገኛል።

ቪዲዮው ለሩሲያ የድል ሰልፍ በዓል እ.አ.አ ግንቦት 9, 2016 በሩሲያ ለሚከበረው ለ2ኛው የዓለም ጦርነት የድል በዓል መታሰብያ ዝግጅት ወታደሮች የመድፍ ልምምድ ሱያደርጉ የሚያሳይም ነው።

ልምምዱ የተደረገውም  ኖቮሲቢርስክ በምትባል በደቡብ ሩሲያ በሳይቤሪያ በምትገኝ ከተማ ውስጥ ሲሆን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም።አርትስ ቲቪ በደሴ በመሀል ከተማ የመንግስትን መድፍ ያሳያል በሚል የተለጠፈው የፌስቡክ ልጥፍ ተመልክቶ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

.     .     .           .            .

 ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው::

እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሐሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::

በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ?እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ::እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::

n
https://miro.medium.com/max/400/0*w5yMtCGA1dJdWsaN
n

ይህ የእውነታ ምርመራ በፔሳቼክ የእውነት መርማሪ በቃሉ ክብሮ እገዛ እና በአርትስ ቲቪ ጋዜጠኛ ረድኤት አበራ ተጽፎ በፔሳቼክ ም/አዘጋጅ ኤደን ብርሃኔ አርትኦት የቀረበ ነው::

አንቀጹ ለህትመት እንዲበቃ ያረጋገጠው ደግሞ የፔሳቼክ ዋ/አዘጋጅ ኤኖክ ናያርኪ ነው::

n
https://miro.medium.com/max/394/0*W96t_rnxwPEV6GVv
n

ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው :: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::

n
https://miro.medium.com/max/60/0*YkqT49Yqdeot06Pp?q=20
n

Follow Us

n
https://miro.medium.com/max/54/0*mDTpdvUOWw1Vdz82?q=20
n

Like Us

n
https://miro.medium.com/max/60/0*3pOdHCE

3ovvbS_?q=20
n

Email Us

ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካ ከዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው::

More in FACT CHECK